መጋቢት ፳፯( ሃያ ሰባት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስአበባ ፖሊስ ኮምሽን ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት ከመጋቢት 20 እስከ የካቲት 10 ቀን 2008 አም 10ኛክፍል ያጠናቀቁ ተመዝጋቢዎች በአካባቢያቸው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ እየቀረቡ እንዲያመለክቱ ጠይቆአል።
በስርአቱ ውስጥ ከሙስናና ብልሹ አስተዳደር ጋር በተያያዘ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሺ የሚቆጠሩ ፖሊሶችና አመራሮች እየተገመገሙ በመባረር ላይ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ክፍተቱን ለመሙላት አዲስ መቅጠር ማስፈለጉን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ተናግረዋል።
በመንግስት ወጪ በቅርቡ የፒኤች ዲ ዲግሪያቸውን የያዙት የትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ፣ ቀደም ሲል የፌዴራል ፖሊስ ኮምሽነር በነበሩበት ወቅት ከፍተኛ ሙስና በማካሄድ የሚታወቁ ሲሆን ፣ የእሳቸው ጉዳይ አስፈጻሚዎች አሁንም ባልተነኩበት ሁኔታ ተራ ወታደሩን በሌብነት አዋርዶ ማባረሩ በሰራዊቱ ውስጥ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሮአል።