ሐምሌ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመለስ ዜናዊን ፋውንዴሽን እንሰራለን በሚል ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችና አርሶአደሮች በነፍስ ወከፍ ከ50 ጀምሮ
እንዲያዋጡ መገደዳቸው በቅርቡ ከተደረገው የደሞዝ ጭማሪ ጋር ተያይዞ የህዝቡን ቁጣ ሊያባብሰው ይችላል ተብሎ በመሰጋቱ ፣ የገንዘብ መሰብሰቡ ሂደት ለጊዜው እንዲቋረጥ
መደረጉን የኢህአዴግ ምንጮች ገልጸዋል።
ፋውንዴሽኑን ለማሰራት ከሚፈለገው ገንዘብ 10 እጥፍ እንደተሰበሰበ የሚነገርለት ፋውንዴሽን በወ/ሮ አዜብ መስፍን የሚመራ ሲሆን እስካሁን ድረስ ወጪና ገቢውን በተመለከተ
ለህዝብ ለማሳወቅ ባለመድፈሩ ከድርጅቱ አባሎች ትችቶች እየቀረቡበት ነው።
በአዲስአበባነዋሪዎችዘንድከፍተኛምሬትያስከተለውይህየገቢማሰባሰቢያበለፉትሁለትሳምንትበድርጅቱደጋፊዎችአማካኝነትየገንዘብማሰባሰቢያደረሰኝበመያዝበከተማውሁሉምቀበሌዎችና
በአንዳንድየወረዳየመንግስትመ/ቤቶችሲዘዋወሩየታየቢሆንም፣ በዚህሰሞንደግሞበደመወዝጭማሪውቅርየተሰኘውህዝብብሶትላለማባባስበሚልለጊዜውዘመቻውእንዲረግብተደርጓል፡፡
ዘመቻው የህዝቡ ምሬት “ቀንሷል” ተብሎ ሲታመን ሊቀጥል እንደሚችል መንጮች አክለው ገልጸዋል።
በቅርቡ የተደረገው የደሞዝ ጭማሪ የኑሮ ውድነቱን እያባባሰው መሆኑን በእየለቱ የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።