ህዳር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሃት) ማዕከላዊ ኮሚቴ እንደገና ስብሰባ መቀሌ ላይ መቀመጡ የታወቀ ሲሆን መንግስታዊ መገናኛ ብዙሃን ስብሰባው መጠናቀቁን አስታውቀዋል።
ከቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕልፈት ወዲህ ሳምንታት እየቆጠረ የቀጠለው የኢሕአዲግ አባል ፓርቲዎች በተለይም የሕወሃትና ኦሕዴድ ሥብሰባ መቋጫ አለማግኘቱንም የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል።
የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ(ሕወሃት) ማዕከላዊ ኮሚቴ ከሕዳር ፭ እስከ ፯ ባካሄደው ስብሰባ አብዛኞቹ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት መገኘታቸው ታውቋል ሆኖም በሕመም ሣቢያ በሲያትል አሜሪካ ሕክምና ላይ የሚገኙት አቶ ስዩም መስፍን በስብሰባው ላይ ሣይገኙ ቀርተዋል።
የቀድሞው ጠ/ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ሕልፈት ወዲህ አንድ ሆኖ መቆም እንደተሳነው የሚነገረው የሕወሃት ቡድን በቅርቡ የተደረጉ ይስልጣን ሽግሽጎችን የሚቃወም ክፍል ከውስጥ በመውጣቱ አንዳንድ ጉዳዮች መቋጫ ሣያገኙ ቀርተዋል የአየር ሃይል አዛዥ ጀነራል ሞላ ኋ/ማሪያም መነሳታቸውንና በሌላ የሕወሃት ጀነራል መሃሪ ዘውዴ መተካታቸውን በሚቃወም የሕወሃት ቡድን በመነሳቱ የአዛዥነት ወንበር በመዋለል ላይ መሆኑ እየተገለጸ ነው በቅርቡ አንድ የሕወሃት ማእከላዊ ኮሚቴ አባል በፈቃዳቸው ከፓርቲው ኋላፊነታቸው ራሳቸውን ማግለላቸው ይታወሳል ሌላው የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ጌታቸው በላይ ከሥረአቱ ተለይተው አሜሪካ መግባታቸውን መዘገባችን አይዘነጋም።