የሕወሃት መሪዎች የመሰረቱት ኩባንያ የሆነውሜጋ ኪነጥበባት ማዕከል በታክስ ማጭበርበር ጥፋተኛ ተባለ

ጥር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሃት) መሪዎች የመሰረቱት ኩባንያ የሆነውሜጋ ኪነጥበባት ማዕከል በታክስ ማጭበርበር ጥፋተኛ ተባለ::     ሆኖም ሥራአስኪያጁ ከ13 ቀናት እሥራት ብኃላ ተለቀዋል::

የኢትዮጵያ ገቢዎችጉምሩክ ባለሥልጣን ታክስ ባለመክፈል በሜጋ ኪነጥበባት ማዕከል እና በስራአስኪያጁ በአቶ ዕቁባይ በርሔ ላይ በመሰረተው ክስ ሥራ አስኪያጁ የሦስትመቶ ሺህ ብር ዋስትና ጠርተው በውጪ ሆነው ሲከራከሩ ቆይተዋል::

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደት ምድብ 10ኛ ወንጀል ችሎት በሕወሐትመሪዎች የተቋቋመው ሜጋ ኪነጥበባት ማዕከል ታክስ ማጭበርበሩ ተረጋግጧልብሎ የጥፋተኝነት ውሳኔ በማሳለፉ አቶ ዕቁባይ በርሔ ፍርድ  እስኪሰጥ በእስርላይ እንዲቆዮ ተደረገዋል::

ፍ/ቤቱ በዛሬው ዕለት ጥር 1 ቀን 2005 በ አቶ ዕቁባይ በርሔ ላይ የአራትዓመት ከአምስት ወራት ጽኑ ዕእስራት እንዲሁም በሜጋ ኪነጥበባት ማዕከል ላይየ125 ሺህ ብር ቅጣት ወሥኗል::

ሆኖም ውሳኔው በሁለት ዓመት ገደብ በመታለፉ አቶ ዕቁባይ በርሔ ከእስር ቤትእንዲለቀቁ ትዕዛዝ ተሰቷል::

በዚህ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረት ሜጋ ኪነጥበብ ማዕከልም የ125 ሺህ ብርቅጣቱን አይከፍልም: አቶ ዕቁባይ በርሔም የአራት ዓመት ከ5 ወራት እሥራቱተፈጻሚ አይሆንባችውም:: ቅጣቱ ተፈጻሚ የሚሆነው በሚቀጥሉት ሁለትዓመታት ሌላ ወንጀል ፈጽመው ሲገኙ ብቻ መሆኑን ከሕግ ባለሙያዎችማብራሪያ