የህዉሃት/ ኢህ አዴግ መንግስት 120 የሱማሊያ እስረኞችን ለሱማሊያ መንግስት ማስረከቡ ተገለጸ

ኢሳት ሰኔ 27/2009

የህዉሃት/ ኢህ አዴግ መንግስት 120 የሱማሊያ እስረኞችን ለሱማሊያ መንግስት ማስረከቡ ተገለጸ።

29ኛውን የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ እየተካፈሉ ያሉት የሱማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀሰን አሊ በቲውተር ገጻቸው የመረጃውን ትክክለኛነት አረጋግጠዋል።  የሱማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን አሊ ሰኞ እለት እንደገለጹት ከሆነ ሃገራቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በገባችው ስምምነት መሰረት 120 የሱማሊያ እስረኞችን ተረክባለች። እስከ ኣስር አመት እና ከዚያ በላይ መታሰራቸው የተገለጸው እስረኞች በምን መመዘኛ ሁኔታ እንደተለቀቁ፤ እንዲሁም የኢህአዴግ መንግስት በአጸፋው ምን ሊያገኝ እንደሚችል የተገለጸ ነገር አለመኖሩ ለማወቅ ተችሏል።

በሜሪካ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከመጣ በኋላ ኢትዮጵያ በሱማሊያ ያላት ሚና እየቀነሰ በመሄዱ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም የአለም አቀፍ ትኩረት ለመሳብ ጥረት እየተደረገ መሆኑ በኢሳት መዘገቡ የሚታወስ ነው።