የህወሃት ድጋፍ ያለው ቡድን በአፋር ስልጣኑን ተቆጣጠረ

ኀዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአፋር ክልል ራሳቸውን ከህወሃት ተጽኖ ለማላቀቅ በሚፈልጉ የአቶ ጣሃ አህመድ ቡድኖችና ህወሃት ከጀርባ ሆኖ በሚመራቸው በአቶ ስዩም አወል መካከል ሲካሄድ የነበረው የስልጣን ሽኩቻ ፣ በህወሃት የሚደገፉት አቶ ስዩም የአፋር ብሄራዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው በመመረጥ አሸንፈዋል።
ከጥቅምት 30 / 2008 ዓ.ም እስከ ሕዳር 03/ 2008 ዓ.ም ድረስ ከቀመሌ ወደ 40 ኪሜ ርቀት በምትገኘዋ በአብዓላ ከተማ ሲካሄድ በቆየው ጉባኤ አቶ ስዩም አወል ተቀናቃኞችን በምርጫ እንዳይሳተፉ በማድረግ ራሳቸውን የፓርቲው ሊቀመንበር፣ አምባሳደር ሓሳን አብዱልቃዲርን ደግሞ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አድርገው አሹመዋል። በጉባኤው ላይ የህወሃቱ አቶ አባይ ጸሃየ፣ አቶ አባይ ወልዱና አቶ ከበደ ጫኔ ተገኝተዋል።
የአፋር የሰብአዊ መብት ድርጅት ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ጋአስ አህመድ ምርጫው የህወሃት የባላይነት የታየበት ነበር ብለዋል