የሃዘን መግለጫ

ቅዳሜ መጋቢት 2, 2009 አም በአዲስ አበባ ከተማ በደረሰው አሰቃቂ አደጋ የመላው የኢሳት ቤተሰብ የተሰማው ሃዘን እየገለጸ፣ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።

በትንሹ ከ60 በላይ ኢትዮጵያውያን ያለቁበትና አሁንም የሟቾቹ ቁጥር እየጨመረ የሚገኘውን ይህን አደጋ በተመለከተ ኢሳት የሶስት ቀና ሃዘን እንዲሆን ወስኗል። ከማክሰኞ መጋቢት 5 ጀምሮ እስከ ሃሙስ መጋቢት 7 2009 በሚቆየው የሃዘን ቀን በኢሳት ማናቸውም ሙዚቃዎች የማይተላለፉ ሲሆን፣ ፕሮግራሞቹ  በሃዘን መግለጫዎች ይታጀባሉ።

ሃዘናቸውን መግለጽ የፈለጉ ኢትዮጵያውያን በቀጣዮቹ ሶስት ቀና በኢሳት የድምፅ መልዕክትን ማኖርና መልዕክቶቻቸውን ማስተላለፍ እንደሚችሉ እየገለጽን በድጋሚ ለመላው ቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ

መጋቢት 4 ፥ 2009