የሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አድማ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል

ግንቦት ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እንደገና የተጀመረውን የኦሮምያ ክልል ተቃውሞ ተከትሎ አድማ በማድረግ ላይ ያሉት የሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ትምህርት እንዲጀምሩ የቀረበላቸውን ማግባቢያ ሳይቀበሉት ቀርተዋል።
ተማሪዎቹ “ጥያቄዎቻችን ይመለሱ፣ የታሰሩ ጓደኞቻችን ይፈቱ” የሚሉ ጥያቄዎችን በማቅረብ ላይ ሲሆኑ፣ የዩኒቨርስቲው ሰራተኞች ተማሪዎችን ለማግባባት ጥረት ቢያድርጉም ተማሪዎች በአቋማቸው ጸንተዋል፡፡