የሃረማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ትምህርት ጀመሩ
(ኢሳት ዜና ማጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ/ም) ወታደሮች ከግቢያቸው እንዲወጡና ያነሱዋቸው የመብት ጥያቄዎች መልስ እንዲያገኙ በመጠየቅ ትምህርታቸውን ለመጀመር ፈቃደኛ ያልሆኑት የሃረማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ዛሬ ትምህርት ካልጀመሩ ከግቢው ለቀው እንዲወጡና ዩኒቨርስቲውም እንደሚዘጋ በወታደራዉ አዛዦች የተነገራቸው ቢሆንም፣ ተማሪዎቹ ትዕዛዙን ባለመቀበል እስከ ጠዋት ድረስ ትምህርት አልጀመሩም ነበር። ይሁን እንጅ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ያደረጉትን ንግግር ተከትሎ ተማሪዎች ትምህርት መጀመራቸውን የገለጸው ዘጋቢያችን፣ የኮማንድ ፖስቱ አባላትም የተማሪዎችን ውሳኔ በማየት እርምጃ ሳይወስዱ ቀርተዋል።
ባለፈው ሳምንት የታሰሩት ተማሪዎች እስከዛሬ አለመፈታታቸውም ታውቋል።