(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 24/2010)የደቡብ አፍሪካ የጸረ አፓርታይድ ታጋይና የቀድሞ የኔልሰን ማንዴላ ባለቤት ወይዘሮ ዊኒ ማንዴላ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።
ዊኒ ማንዴላ ከዚህ አለም በሞት የተለዩት በ81 አመታቸው መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።
ኔልሰን ማንዴላ ከ27 አመታት በኋላ ከእስር ሲለቀቁ ዊኒ ማንዴላ ከነጻናአ ታጋዩ ጋር ግንኑነታቸው ስላልተቋረጠ ዝናቸው ከፍተኛ እንደነበር ዘገባው አስታውሷል።
በኋላ ላይ ግን ከኔልሰን ማንዴላ ጋር ሲለያዩ በፖለቲካም ሆነ በማህበራዊ ሕይወታቸው ዝናቸው እየቀነሰ መምጣቱ ተነግሯል።
የዊኒ ማንዴላን አሟሟት በተመለከተ ከቤተሰቦቻቸው መግለጫ እንደሚሰጥም ይጠበቃል።