ወ/ሮ ንግስት ወንድይፍራው ታሰረች

ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወ/ሮ ንግስት በደቡብ ክልል የምርጫ ቅስቀሳ አድርጋ ስትመለስ መታሰሩዋን ባለቤቱዋ ለኢሳት የገለጸ ሲሆን፣ የ3 አመት ህጻን ልጇም አብራ ከታሰረች በሁዋላ እንደመለሱለት
አክሏል።
ለምርጫ ቅስቀሳ ወጥተው የነበሩ ብዙ ወጣቶች እየተፈለጉ መሆኑን መረጃው እንደደረሳትና እርሱዋም እንደምትታሰር አውቃ ወደ አዲስ አበባ መመለሱዋን ባለቤቱ ገልጿል።
በአዲስ አበባ አይ ኤስ ኤስ የጠባለው አሸባሪ ቡድን በሊቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደውን አሰቃቂ እርምጃ ለማውገዝ የወጡ ወጣቶች፣ አጋጣሚውን በመጠቀም በመንግስት ላይ ተቃውሞአቸውን ማሰማታቸው ይታወቃል።
ተቃውሞው እንዳበቃ በርካታ ወጣቶች ተይዘው ታስረዋል። አሁንም እየታደኑ ያሉ በርካታ ወጣቶች ያሉ ሲሆን፣ ምናልባትም የምርጫው የመጨረሻ ውጤት እስከሚገለጥበት ቀን ድረስ ታስረው ሊቆዩ ይችላሉ።