ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በወረ ጃርሶ ወረዳ በሚገኙ በፋጂ ኢጀርሳ፣ ላንቱ ወላርጊ እና ምእራብ ኮርጎጎ ቀበሌዎች የሚኖሩ ከ300 በላይ አርሶአደሮች ከሰኔ 28 ቀን 2007 ዓም ጀምሮ ኢጀርሳ መንደር ውስጥ በሚገኝ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ታስረው እየተደበደቡ መሆኑን ቤተሰቦቻቸውና እስራቱን ለማምለጥ የተደበቁ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
አርሶ አደሮቹ የታሰሩት ሻሾ አንበሳ እና ዘላለም ጊዲሳ የተባሉ ሁለት ወጣቶች ከመንግስት የሚደርስባቸውን ጥቃት በመሸሽ መሸፈታቸው ከተነገረ በሁዋላ ነው። አርሶአደሮቹ ለሽፍቶቹ ምግብ ታቀብላላችሁ፣ መደበቂያ ቦታም ትሰጣላችሁ በሚል ከ8 ቀበሌዎች ተሰብስበው ኤጀርሳ ትምህርት ቤት ውስጥ ከታሰሩ በሁዋላ፣ ልብሶቻቸውን እንዲያወልቁ ተነግሮአቸው በፌደራል ፖሊስ አባላት ክፉኛ ተደብድበዋል። ቤተሰቦቻቸው ምግብና ውሃ እንዳይወስዱላቸውም ተከልክለዋል። በህጋዊ መንገድ ያስመዘገቡ የግል የጦር መሳሪያቸውም ተወስዶባቸዋል።
ነሃሴ 5 ቀን በተፈጸመው ቢቂ ፣ ድርቤ፣ ትርፉና ኩልኪ ሴቶች ናቸው።
አርሶአደሮቹ ከወር በላይ ለሆነ ጊዜ በመታሰራቸው የእርሻ ስራቸውን ለመስራት አልቻሉም። ቤተሰቦቻቸውም በየደረጃው ላሉ ባለስልጣናት አቤት ቢሉም መፍትሄ ሊያገኙ አልቻሉም።
በዚህ ዞን አንድ የወረዳ ባለስልጣን መሳሪያህን ደብቀሃል ያለውን አርሶደአደር በሚስቱ ፊት እርቃኑን አቁሞ ጸያፍ ድርጊት እንደፈጸመ ኢሳት መዘገቡ ይታወቃል።