ከ 1 ሺህ 500 በላይ የወለኔ ተወላጆች አዲስ አበባ ከተማ እንዳይገቡ ተከለከሉ

ሰኔ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- የወለኔ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ወሕዴፓ) እሑድ ሰኔ 17 ቀን 2004 ዓ.ም. በመሀል አምባ የጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ በፖሊስ ኃይል  ተበተነ፡፡

ስብሰባውን ለመሳተፍ ከአዲስ አበባና ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተሰባስበው የመጡ የፓርቲው ደጋፊና የብሔረሰቡ ተወላጆች ወደ ከተማው እንዳይገቡ በክልሉ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ታግደው ወደመጡበት እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡

ፓርቲው ፤ ከብሔረሰቡ ተወላጆች፣ ከአባላቱና ከደጋፊዎቹ ጋር ሕዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ  በሚል ከአዲስ አበባ  በ119 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘውና  የደቡብ  ክልል ጉራጌ ዞን፣ ገደባኖ ቡታዘር ወለኔ ወረዳ አካል በሆነችው “ መሀል አምባ” ከተማ  የሕዝባዊ ስብሰባ ጥሪ አድርጐ ነበር፡፡

በዚህ ጥሪ መሠረት  ነው በወረዳው ውስጥ ከሚገኙ 34 የገጠር ቀበሌ ገበሬ ማኅበራት የተውጣጡ  ከ 1 ሺህ 500 በላይ የብሄረሰቡ አባላት  ሰሞኑን ወደ አዲስ አበባ  የተጓዙት።

ይሁንና   ከረዥም ጉዞ በሁዋላ  ወደ አዲስ አበባ  ሲደርሱ ፤ስብሰባቸውን  እንዳያደርጉ ተከልክለው በፀጥታ ኃይሎች ተበትነዋል፡፡

እነኚሁ ከሺህ አምስት መቶ በላይ የሆኑት የወለኔ ተወላጆች ከመቶ ኪሎ ሜትር በላይ ተጉዘው  ወደ አዲስ አበባ ሲደርሱ፤በክልሉ ፈጥኖ ደራሽ የፖሊስ ኃይልና በወረዳው ፀጥታ ኃይሎች ወደ ከተማው እንዳይገቡ ከግማሽ ቀን በላይ ታግደው ቆይተው ነበር፡፡

ወደ ከተማው መግባት በመከልከላቸውም ፤ ስብሰባውን ለማካሄድ ሳይችሉ ቀርተው ወደየመጡበት ተመልሰዋል፡፡

የወሕዴፓ ሊቀመንበር አቶ አብዲ ተማም በስፍራው ከተሳታፊዎች ጋር ወደ ከተማው መግባት ለተከለከለው የጋዜጠኞች ቡድን በሰጡት መግለጫ፣ ድርጅታቸው ሕግና ሥርዓትን ተከትሎ ስብሰባ ለማካሄድ ክልሉን፣ ዞኑንና የወረዳውን አስተዳደር ጠይቆ ሕዝባዊ ጥሪ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

በዚህ መሠረት ቁጥራቸው ከ1,500 በላይ የሚሆኑ ተሳታፊዎች ከተለያዩ ክልሎች  ተሰባስበው ወደ መዲናዋ ሲደርሱ፤ “ወደ ከተማው መግባት አትችሉም” መባላቸው ፈጽሞ ያልጠበቁት ጉዳይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ከ20 በሚበልጡ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችና በግል ተሽከርካሪዎች ሕዝባዊ ስብሰባውን ለመሳተፍ 119 (በዛ) ኪሎ ሜትር አቋርጠው የመጡ ተሳታፊዎችና የመገናኛ ብዙኅን ባለሙያዎች፣ መሀል አምባ የገጠር ከተማ መዳረሻ ኢሎ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ላይ፤ በፀጥታ ኃይሎች መታገዳቸውን የሪፖርተር ዘገባ ያመለክታል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide