ከድንበር ማካለል ጋር በተያያዘ ጋብ ብሎ የሰነበተው የኮሬና የጉጂ ማህበረሰብ ግጭት እንደገና አገረሸ

ከድንበር ማካለል ጋር በተያያዘ ጋብ ብሎ የሰነበተው የኮሬና የጉጂ ማህበረሰብ ግጭት እንደገና አገረሸ
(ኢሳት ዜና የካቲት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) ለሳምንታት ጋብ ብሎ የሰነበተዉና በአካባቢው የአገዛዙ ካድሬዎች አማካኝነት መለኮሱን ነዋሪዎች የሚናገሩት የኮሬና ጉጂ ኦሮሞ ማህበረሰብ ግጭት እንደገና በማገርሸቱ፣ የዜጎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
ለግጭቱ ማገርሸት አሁንም የአካባቢዉ ህብረተሰብ አገዛዙን ተጠያቂ አድርጓል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ከለላ በማድረግ የሁለቱ ክልሎች ድንበር በፍጥነት መካከል አለበት በሚል እንቅስቃሴ መጀሩን ተከትሎ ጋብ ብሎ የሰነበተው ግጭት እንደገና አገርሽቷል። እስካሁን ባለው መረጃ በኮሬ በኩል ጀሎ ቀበሌ ላይ የአንድ ሰው ህይወት ሲጠፋ፣ ዳቡልቶ ቀበሌ ላይም እንዲሁ የአንድ አርሶአደር ህይወት ጠፍቷል።
ከአማሮ ወረዳ ወደ ዲላ ሲጓዝ በነበረ አይሱዙ መኪና ላይ በተተኮሰ ጥይትም ሶስት ሰዎች ቆስለዋል።
የድንበር ማካለሉን ተከትሎ በኮሬ፣ በቡርጅና ጉጂ ማህበረሰቦች መካከል የተጀመረው ግጭት 8ኛ ወሩን ይዟል። በግጭቱም የበርካተ ዘጎች ህይወት ጠፍቷል።