ነሃሴ ፳፪(ሃያሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደሚሉት በመቀሌ፣ ባህር ዳርና በተለያዩ የጤና ተቋማት የሚሰሩ ሙያተኞች
መንግስት በቅርቡ ያደረገው የደሞዝ ጭማሪ ሙያችንን ግምት ውስጥ ያስገባ አይደለም በማለት ስራቸውን እየሰሩ ቀይ ሪባን በመልበስ ተቃውሞ እንደሚጀምሩ
ታውቋል።ዲፕሎማ እንዳላቸው የሚገልጹት ሰራተኞች መንግስት የስራ ዝርዝራቸውን ለይቶ እንዲያስቀምጥላቸውም ይጠይቃሉ።
በሀረር ከተማ ደግሞ ከ400 ያላነሱ በጽዳት ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች መዘጋጃው የደሞዝ ማሻሻያ እንዲያደርግላቸው ለመጠየቅ ለሁለተኛ ጊዜ ባለፈው ሳምንት
የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። ዘጋቢያችን እንደሚለው ሰራተኞቹ እስካሁን ተስፋ የሚሰጥ መልስ አላገኙም።