ከእስራኤል አገር በደህንነት ሙያ ሰልጥነው ስራ ከጀመሩት መካከል የተወሰኑ ሰራተኞች መታሰራቸው ታወቀ

ሰኔ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ከእሰራኤል አገር በደህህነት ሙያ ሰልጥነው በቴሌኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት  እና በተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት ከተመደቡት መካከል ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የደህንነት አባሎች ታሰሩ።

አባሎቹ የታሰሩት መረጃውን ለኢሳት አቀብላችሁዋል በሚል ተጠርጥረው ነው። እስካሁን ምን ያክል የደህንነት ሰራተኞች ተይዘው እንደታሰሩ አልታወቀም። ኢሳት ከአስተማማኝ የደህንነት ምንጮች ባገኘው መረጃ ስልጠናውን አጠናቀው ወደ አገራቸው ከተመለሱት 987 ሰዎች መካከል ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑት የአንድ ብሄር ተወላጆች ሲሆኑ፣ አብዛኞቹ በተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት ተመድበዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ በኢትዮጵያ የእስራኤል ኢምባሲን ለማነጋገር ሙከራ አድርገን ሳይሳካ ቀርቷል።