ከኤርትራ ጋር በሚዋሰኑ ቦታዎች ተጨማሪ ራዳሮች እየተተከሉ ነው

ታኅሣሥ ፲ (አሥር)ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ህወሃት/ኢህአዴግ የሚመራው መንግስት ከኤርትራ ጋር በሚዋሰኑ ድንበሮች አካባቢ ዘመናዊ ካሜራዎችንና ራዳሮችን እያስተከለ ነው። በሰሜን የአገሪቱ ክፍሎች በቅርቡ ዘመናዊ ራዳሮችና የርቀት ካሜራዎች እጅግ ውድ በሆነ ዋጋ ተገዝተው የተተከሉ ሲሆን፣ ትናንት እሁድ ደግሞ በአፋር ክልል በእንድፎና አዳይቱ በሚባሉ ከተሞች መሃል ላይ የራዳር ተከላው ሲከናወን ውሎአል።

የሩሲያና ቻይና ስሪት የሆኑት መሳሪያዎች በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የወጣባቸው ናቸው። በቅርቡ ከ10 በላይ የሩሲያ ወታደራዊ አዛዦች ወደ አዲስ አበባ መግባታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።