መስከረም ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባ መስተዳዳር በንፋስ ስልከ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዜሮ አንድ ሱቂ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከመስከረም 19 ጀምሮ እያካሄደ ባለው ህገወጥ ያላቸውን ቤቶች በማፍረስ እርምጃ ከ1000 ያላነሱ ነዋሪዎችን የያዙ ከ130 በላይ ቤቶች እየፈረሱ ነው።
በመንግስት ድርጊት በርካታ ህጻናት ሲያልቅሱ፣ ቋሚዎች ሙታንን ለመቅበር ሲቸገሩ፣ አሮጊቶችና ሽማግሊዎች መጠጊያ አጥተው ለብርድና ለዝናብ መዳረጋቸውን ቤታቸው የፈረሰባቸው ሰዎች ለኢሳት ገልጠዋል።
አቶ ፍቃዱ ማንደፍሮ እንዳሉት 50 የሚሆኑ ፖሊሶችና የጎዳና ተዳዳሪዎች በአካባቢው መጥተው ጉዳት እንዳደረሱባቸው ገልጠዋል
አቶ ፈቃዱ እንደሚሉት መንግስት በጻፈላቸው ትብብር በግላቸው የመሰረተ ልማቶችን መዘርጋታቸውን ገልጸዋል
ሌላው ተፈናቃይ አቶ አለሙ በንቲ በበኩላቸው በርካታ ህጻናቶችና አራሶች ሳይቀሩ ውጭ እያደሩ ነው መሆኑን ተናግረዋል
አቶ ወርቁ ማተቤ በበኩላቸው የሚደርስባቸውን በደል “ቤታችንም ሰውነታችንንም” ማዳን አልቻልንም በማለት ይገልጡታል
አቶ አለሙ እርሳቸው በሚኖሩበት አካባቢ መንታ ወልደው ሜዳ ላይ የተጣሉ እናቶች መኖራቸውን በሀዘን ተናግረዋል
በጉዳዩ ዙሪያ የአዲስ አበባ መስተዳድር ሃለፊዎችን ለማግኘት ጥረት ብናደርግም አልተሳካልንም።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide