ሰኔ ፳፬ ( ሃያ አራት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ወረዳ አንድ አካባቢ በህገወጥ መንገድ ተሰርተዋል የተባሉ ቤቶችን ለማፍረስ የተጀመረው ዘመቻ እንደቀጠለ ባለበት በዚህ ወቅት፣ በምሽት እየታደኑ የሚገደሉ ሰዎች ቁጥር መጨመሩንም የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።
ነዋሪዎች እንደሚሉት ትናንት ምሽት ፌደራል ፖሊሶች አንድ ቄስ ገድለዋል። እስካሁን ለማረጋጋጥ ባንችልም ሌላም አንድ ቄስ ክፉኛ ተጎድተው በሞትና በህይወት መካከል እንደነበሩ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ወታደሮች ወደ አካባቢው ማንም ሰው እንዳይጠጋ በመከልከላቸው የሟቾችን ቁጥር በትክክል ማወቅ አልተቻለም። ከገልለተኛ ወገን ማረጋጋጥ ባይቻልም አንዳንድ ሰዎች ግን በእስካሁኑ ተቃውሞ ከ10 ያላነሱ ሰዎች ተገድለዋል ይላሉ።
ማታ ማታ ቤተ ለቤት በሚደረግ ፍተሻ በርካታ ወጣቶች ተይዘው ወደ ዝዋይ እስር ቤት ተወስደዋል።