ከሰሞኑ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የታሰረ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ተፈረደበት

ሚያዝያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያና ደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግድያ ለመቃወም በተጠራ ሰልፍ ላይ ከቤቱ ተወስዶ የታሰረው የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው አቶ ስንታየሁ ቸኮል  ስድስትወርእንደተፈረደበት ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል።

ጋዜጣው እንደሚለው ግንቦት 3/2007 ዓ.ምቄራየመጀመሪያ ፍርድቤት የቀረበው አቶ ስንታየሁ ፖሊስ በሰልፉ ወቅት ድንጋይ ወርወሯል በሚል በቀረበበትክስ  የስድስት ወር እስር ተፈርዶበታል፡፡

አቶስንታየሁመቃወሚያና የክስ ማቅለያ እንዲያቀርብ ተጠይቆ ‹‹የከሰሰኝኢህአዴግነው፡፡እየመሰከሩብኝያሉትምኢህአዴጎችናቸው፡፡የወሰነብኝምኢህአዴግነው፡፡በመሆኑምፍትህአገኛለሁብዬመቃወሚያምማቅለያምአላቀርብም›› በሚልመቃወሚም ማቅለያም ሳያቀርብ

ተፈርዶበታል።