ከረዢም አመታት በፊት የተጀመረው የባህርዳር ሞጣ ብቸና መንገድ አሁንም ችግር እየፈጠረ መሆኑ ተነገረ፡፡

ነኅሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአመታት በፊት ተጀምሮ በማዝገም ላይ ያለው የባህርዳር ሞጣ ደጀን መንገድ አሁንም በንግድ እንቅስቃሴያቸው ላይ ከፍተኛ ችግር እየፈጠረባቸው መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ በትራንስፖት ቢሮ የትራንስፖርት አገልግሎት የስምሪት ተተኪ የስራ ሂደት ውስጥ የሚገኙ ባለሙያ እንደተናገሩት መንገዱ በተደጋጋሚ በመበላሸቱ እና ለረዢም ጊዜ ባለመሰራቱ ህብረተሰቡ መቸገሩን ገልጸው፤ለመንገድ ስራ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤቶች ስራውን እንዲያጠናቅቁ በተደጋጋሚ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ቢጻፍላቸውም ስራውን ለማጠናቀቅ አልቻሉም።
ባለሙያው በተጨማሪ እንደተናገሩት የስራውን መጠናቀቅ ተከታትሎ ለማስፈጸም ሃላፊነቱን የወሰደው የፌደራል ትራንስፖርት ሚኒስቴር የህዝቡን ተደጋጋሚ ቅሬታ ሰምቶ እንዳልሰማ መሆኑ የመልካም አስተዳደር ችግር እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
ከአዲስ አበባ በቡሬ ባህርዳር አሁን የሚያገለግለው የአስፓልት መንገድ 565 ኪሎ ሜትር ሲሆን ከአዲስ አበባ በሞጣ ባህርዳር ግን አንድ መቶ ኪሎ ሜትር የሚቀንስ በመሆኑ ነጋዴዎች የሸቀጥ ጭነታቸውን በሞጣ በኩል በመጫን በትራንስፖርት መቀነስ ምክንያት የሚኖረውን የኑሮ ውድነት በመጠኑ ለማገዝ የሚያስችል የንግድ እንቅስቃሴ ለመፍጠር የሚችሉበትን ዕድል እንዳላገኙ ነጋዴዎች ይናገራሉ፡፡
በተለይ ከደጀን ብቸና በሚወስደው መንገድ ብቸና ከተማ አካባቢ የሚገኘው የሰዋ ወንዝ ድልድይ ባለፈው የክረምቱ ወራት ወቅት መሰበሩ በርካታ ችግሮችን እንዲያሳልፉ መገደዳቸውን የሚናገሩት የብቸና ከተማ ነዋሪዎች፣ የዚህ መስመር የአስፓልት መንገድ ለምን በተያዘለት ጊዜ እንደማይጠናቀቅ ሁሌም እንደሚገረሙ ተናግረዋል፡፡
ከደጀን ፈለገ ብርሃን ያለው የመንገድ ፕሮጀክት ሳትኮን በሚባል ሃገር በቀል የመንገድ ስራ ተቋራጭ እየተከናወነ ቢገኝም የጥራቱ ጉዳይ አሳሳቢ ከመሆኑና በአካባቢው የተሰሩት ድልድዮች ከማነሳቸው የተነሳ በስራቸው ጎርፍ ማሳለፍ አቅቷቸው በላያቸው ላይ እየፈሰሰ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ያሰማሉ፡፡ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሳምሶን ወንድሙ ከሁለት አመት በፊት ባደረጉት ገለጻ ከደጀን ፈለገ ብርሃን ድረስ ያለው የመንገድ ፕሮጀክት በቶሎ እንደሚጠናቀቅ አስታውሰው፥ ከዘማ ወንዝ እስከ ባህርዳር ድረስ ያለው የመንገድ ፕሮጀክትም በ2006 ይጀመራል በማለት በነሃሴ ወር 2005 ዓ.ም ቃል ቢገቡም የመንገድ ስራው ፐሮጀክት በዚህ አመት ተጀምሮ በመጓተት ላይ መሆኑን ቅሬታ አቅራቢዎች ይናገራሉ፡፡
የሳትኮን ባለቤት አቶ ሳሙ ኤል ተኽላይ የሰራተኞችን ደመ ዎዝ ለወራት በመ ከልከልና በማ ሰቃየት፣የመ ኪ ና ክራይ በወቅቱ ባለመ ክፈልና ስራን በማጓተት በተደጋጋሚ ቢከሰሱም፣ ገዢ ው ፓ ርቲ ለሁሉም ፕሮጀክቶቻቸው ከለላ በመ ስጠት ከተጠ ያቂነት ነጻ ሲያደርጋቸው መ ቆየቱን ታዛቢዎ ች ይናገራሉ፡፡
ሳትኮን ኮንስትራክሽን በህውሃት መንግስት ታቅፈው በአዲስ አበባ በስፋት ከሚንቀሳቀሱ የህወሃት ደጋፊ የሪልስቴት ባለሃብቶች መካከል አንዱ ሲሆን፣ በርካታ የግንባታ ስራዎችን ያለ ጨረታ ይወስዳል። አምባሳደር ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ አካካየ ሪልስቴት፣ክንዴ ሃጎስ ሪልስቴት፣ ተክለብርሃን አምባዬ ሪልስቴት፣ ጊፍት ትሬዲንግ፣ ሲቲ ዋይድ ኢንጂነሪንግ፣ አሴ ትሬዲንግ፣ ስብሃቱ እና ቤተሰቡ ትሬዲንግ ከህወሃት ጋር በቅርብ የሚሰሩ የሪል ስቴት ኩባንያዎች ናቸው።