ከማኑፋክቸሪን ዘርፍ ከእቅድ በታች ገቢ መገኘቱን የኢንዱስትሪ ሚንስቴር ገለጸ

ኢሳት (ግንቦት 2 ፥ 2008)

በተያዘው በጀት አመት ከማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ወደ 500 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 290 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 290 ሚሊዮን ዶላር ብቻ መገኘቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ማከስኞች አስታውቋል።

መንግስት የውጭ ንግዱን ልዩ ድጋፍ በመስጠት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪን ለማግኘት እቅድ ቢይዝም የታሰበው ገቢ ሊገኝ አለመቻሉንም ባለስልጣናት በመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።

በተያዘው በጀት አመት ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የተለያዩ የማኑፋክቸሪንግ ምርቶችን ለማምረት ጥረት ቢደረግም ለማሳከት የተቻለው 54 ቢሊዮን ብር አካባቢ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በአመታዊ ሪፖርቱ አስፍሯል።

በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መንግስት ከማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ወደ አራት ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት እቅድን መንደፉ ይታወሳል።

ይሁንና፣ ዘርፉ እያስመዘገበ ያለው ገቢ ከእቅዱ ጋር ሲነጻጸር እጅግ ዝቅተኛ ሲሆን፣ ገቢውም በውጭ ምንዛሪ እጥረቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች አስረድተዋል።

የውጭ ንግድ ገቢ ማሽቆልቆልን ተከትሎም መንግስት በዘርፉ ከተሰማሩ ተቋማት ላይ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ እንደሚገኝም ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል።