ከሚኒስትሮች ውጭ ያሉ ሁሉ በፖለቲካ ስብሰባዎች ላይ ሞባይል መያዝ እንደሌለባቸው አቶ በረከት ተናገሩ

ጥቅምት ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ በረከት ስምኦን ” የኢሳት ዘጋቢዎችን መቆጣጠር አልተቻለም፣ በውስጣችን ያሉ ሃይሎች ጣሉን” ያሉ ሲሆን፣ ከሚኒስትሮች በስተቀር የደህንነት ሃይሎችም ሆኑ ጋዜጠኞች በፖለቲካ ስብሰባ ላይ ሞባይል ይዘው እንዳይገቡ እንደከለከሉ ትእዛዝ አስተላልፈዋል።

አቶ በረከት ከዚህ ቀደም እርሳቸውንና ድርጅታቸውን የተመለከቱ መረጃዎች በኢሳት ተደጋግሞ መውጣት እንዳበሳጫው የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።

የኢህአዴግን ምክር ቤት ስብሰባዎች ለመዘገብ የተጠሩ ጋዜጠኞችና ስብሰባውን እንዲከታተሉ የተጠሩ የደህንነት ሰራተኞች ከዚህ ቀደም ባልተለመደ ሁኔታ ሞባይሎቻቸውን እያስቀመጡ መሳተፍ ጀምረዋል። ኢሳት ተመሳሳይ ትእዛዝ ቀደም ብሎም መተላለፉን መዘገቡ ይታወሳል።