(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 1/2011)የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር /ኦብነግ/ ዛሬ በይፋ ትጥቅ መፍታቱ ተገለጸ።
ከሁለት ወራት በፊት ወደ ሀገር የገባው ኦብነግ በሰላማዊ ትግሉ ለመቀጠል መዘጋጀቱን ሊቀመንበሩ አድሚራል መሃመድ ኡመር አስታውቀዋል።
ዛሬ በጅጅጋ ከተማ በተከናወነው ስነስርዓት የኦብነግ ሰራዊት ትጥቁን በመፍታት በክልሉ መንግስት ስር እንደሚሆን ተገልጿል።
የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ መሃመድ ኡመር የኦብነግ ትጥቅ መፍታት ለሶማሌ ክልል ሰላምና እድገት ወሳኝ ምዕራፍ ነው ብለዋል።
በትጥቅ ማስፈታት ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት የሚዲያ አማካሪ አቶ አብዱላሂ ሀሰን አነጋግረናል።