ኦህዴድ በየደረጃው ያሉ አመራሪዎችን ለአስቸኳይ ስብሰባ ጠራ

ነሃሴ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሁሉም የኦሮምያ ክልሎች  በሚገኙ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች፣ የግብርና ዋና እና ምክትል

ሃላፊዎች፣ የሴቶች ጽ/ቤት ፣ መሬት ጥበቃ ፣ ሲቪል ሰርቪስ እና መልካም አስተዳደር ፣ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፣ ውሃና ማእድን፣ ገጠር መንገድ ፣ ጥቃቅንና

አነስተኛ ጽ/ቤት ፣ ገንዘብና ኢኮኖሚ ፣  ትምህርት/ጽ/ቤት፣ እና  የወጣቶችና ስፖርት ሃላፊዎች ከነገ ጀምሮ ለአስቸኳይ ስብሰባ እንዲከቱ ተደርጓል። አስቸኳይ

ስበሰባው ለምን እንዳስፈለገ ባይታወቅም፣ ሰሞኑን ኢህአዴግ እያደረገ ካለው ግምገማ እንዲሁም በድርጅቱ ውስጥ የሚታዩትን ችግሮች ከመገምገም ጋር ሊያያዝ

እንደሚችል ምንጮች ጠቁመዋል።