መጋቢት ፳፪( ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሃት ኩባንያዎችና አባላት በደቡብ አሞ ዞን ከፍተኛ መሪዎች መውሰዳቸው ከተጋለጠ በሁዋላ በቁጥጥር ስር የዋሉት የደቡበ አሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ም/ሊቀመንበርና የዞኑ ጽ/ቤት ቤት ኃላፊ አቶ ዓለማየሁ መኮንን፣ የፓርቲው አባል አቶ አብረሃም ብዙነህ እንዲሁም አቶ ስለሺ ጌታቸው ከጅንካ እስር ቤት ወደ አዋሳ እስር ቤት እንዲዛውሩ ከተደርጉ በሁዋላ ረቡእ ክሰአት በሁዋላ ፍርድ ቤት ቀርበው የ 14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል።
እስረኞቹ ወደ አዋሳ መዛውራቸው በቤተሰቦቻቸው እንዳይጠየቁ ለማደረግ ሆን ተብሎ የተደርገ ነው በማለት ተቃውሞ ቢያሰሙም የሚስማቸው አላገኙም።ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የጠየቀውን የጊዜ ቀጥሮ ፈቅዶአል።
የድርጅቱ የዞን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ‹‹ እስራቱን ህገወጥና ከድርጅታችን የትግል መስመር በወጣ መልኩ በፈጠራ የሽብርተኝነት ታፔላ የድርጅታችን መሪ በመክሰስ አባላቱን ለማስፈራራት እና የድርጅታችን እንቅስቃሴ ለማፈንና ለማዳከም ›› የታቀደ ነው በማለት ካወገዘ በሁዋላ ‹‹ ወደ ሰላማዊ ትግሉ ስንገባ ከዚህ የበለጠ መስዋዕትነት እንደሚጠይቅ አውቀን በመሆኑ ፣ይህ ከተያያዝነው ሰላማዊ ትግላችን ወደኋላ አይስበንም፣ ሰላማዊ ትግላችን እስከድል ድረስ ይቀጥላል›› ብሎአል ። የጂንካ ነዋሪዎች እስረኞቹ ወደ አዋሳ መዛወር የለባቸውም በሚል በፖሊስ ጣቢያው አካባቢ በመግኘት ተቃውሞአቸውን እሰከምሸት ድረስ ሲገልጡ አምሽተዋል።
በህገወጥ የታሰሩ የሰላማዊ ጓዶቻችን በሚመለከት በቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለበትና ትግሉንም ከነበረበት አጠናክሮ ለመቀጠል በሚያስችለው ዘዴ ላይ እየተወያየና ከድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት ጋር እየተነጋገረ መሆኑን የገለጠው ድርጅቱ ፣ በቀጣይ ለሚደርገው የሰላማዊ ተቃውሞ ትግል የአካባቢው ህዝብ ተዘጋጅቶ እንዲጠብቀውና በተለያየ ዘርፍ የተሰማሩ የዞኑ ነዋሪዎች በሙሉ በየተለመደውን ትብብርና ድጋፍ እንዲያደርጉ ፣ በተለይም የታሳሪዎችን ቤተሰብ በመጎብኘትና በማበረታታት እንዲተጋ የትግል ትብብር ጥሪ አቅርቧል ፡፡
በዞኑ የሚታየው የመሬት ቅርምት የአካባቢውን ህዝብ ማስቆጣቱ ታውቁዋል። በተለይ የህወሃት ድርጅቶችና ደጋፊዎች ወደ አካባቢው ዝር ሳይሉ መሬት እየዘርፉ፣ ከባንክ በድር በመውሰድ የአካባቢውን ነዋሪች እያደኽዩ ነው የሚለው መረጃ ከወጣ ጀምሮ ፣ ነዋሪዎችና የዞኑ ተወላጅ ተቆርቁዋሪ ባለስልጣናት እየተነጋገሩበት ነው። እነ አቶ አለማየሁ መረጃውን ለኢሳት አቀብለዋል በሚል ጥርጣሬ ሳይያዙ እንዳልቀረና የሽብር ክስ ሊክፍተባቸው እንደሚችል፣ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች ገልጸዋል።