ሐምሌ ፲፫ ( አሥራ ሦስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አርበኞች ግንቦት 7ትን ሊቀላቀሉ ሲሉ መንገድ ላይ ተይዘዋል በሚል ክስ የተመሰረተባቸው ብርሃኑ ተክለያሬድ ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማው እንዲሁም የግንባሩ አባል ነው የተባለው ደሴ ካሳይ ፍርድ ቤት ቀርበው ጥፋተኞች ተብለዋል፡፡
14ኛው ወንጀል ችሎት ውሳኔውን ያስተላለፈው ተከሳሾች የመከላከያ ምስክሮችን ባላቀረቡበት ሁኔታ ነው። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ የተለያዩ ታዋቂ ሰዎችንና የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናትን በመከላከያ ምስክርነት ለማቅረብ አስመዝግበው የነበረ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ ምስክሮቻችሁን አቅርባችሁ ማሰማት አትችሉም ብሎአቸዋል።
ተከሳሾች በጸረ ሽብር አዋጁ አንቀጽ 652/2001 መሰረት ሃምሌ 22 ቀን 2008 ዓም የፍርድ ውሳኔ እንደሚያገኙ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።