እስራኤል ጎንደር የሚገኙ ቤተእስራኤላውያንን ለማስወጣት እንቅስቃሴ ጀመረች

ሐም ( ስድስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዘ ጀሩሳሌም ፖስት እንደዘገበው አዲስ አበባ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ በጎንደር የሚገኙ ከ6 ሺ ያላነሱ ቤተእስራኤላውያንን ለማስወጣት እየሞከረ ነው።

ቤተእስራኤላውያን በአንድ አካባቢ ተሰባስበው ጥበቃ እየተደረገላቸው መሆኑን የእስራኤል የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል።

ጋዜጣው ከትግራይ ክልል የተነሱ ታጣቂዎች ወደ አማራ ክልል በመግባት ሰዎችን አፍነው ለመውሰድ መሞከራቸው ለግጭቱ መንስኤ መሆኑን ዘግቧል።