(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 17/2009)በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ንኡስ ኮሚቴ ተቀባይነት ያገኘውና በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩና ሁሉን አቀፍ አስተዳደር እንዲኖር የሚያስችለው ኤች አር 128 የተሰኘው የውሳኔ ሀሳብ ለአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ሊቀርብ ነው።
ይህ የህግ ረቂቅ የባለስልጣናት ሀብትና ንብረት እንዲያዝ አሜሪካ ወይም ምእራብ ሀገራት እንዳይገቡ የሚጠይቅና ባለስልጣናቱ በስርአቱ ባላቸው ስልጣንም ሆነ በግላቸው የሚጠየቁበት እንደሆነ ተገልጿል።
ኤች አር 128 የተሰኘው የውሳኔ ሀሳብ በአሜሪካ ሪፐብሊካን የምክር ቤት አባል በሆኑት ኮንግረስ ማን ክሪስ ስሚዝ አማካኝነት ቀርቦ ወደ 55 በሚደርሱ የዲሞክራትና ሪፐብሊካን የምክር ቤት አባላት ተቀባይነት እንዳገኘም ተጠቅሷል።
ይህ የህግ ረቂቅ የባለስልጣናት ሀብትና ንብረት እንዲያዝ አሜሪካ ወይም ምእራብ ሀገራት እንዳይገቡ የሚጠይቅና ባለስልጣናቱ በስርአቱ ባላቸው ስልጣንም ሆነ በግላቸው የሚጠየቁበት እንደሆነ ተገልጿል።
በዚህ ረቂቅ ላይ ከጸደቁት የህግ ሀሳቦች መካከል የሰርጊ ማግኔትስኪ አክት አንደኛው እንደሆነ የጠቀሱት ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ የሰርጊ ማግኔትስኪ አክት በሩሲያ ባለስልጣናት ላይ ተግባራዊ እንዲደረግ በአሜሪካ ምክር ቤት የጸደቀ ህግ እንደሆነም ተናግረዋል ።
ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ ይህንን ኤች አር 128 የውሳኔ ሀሳብ በአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት እንዲጸድቅ ከፍተኛ ዘመቻ ከሚያደርጉት ኢትዮጵያውያን መካከል ናቸው።
ይህ የውሳኔ ሀሳብ ለምክር ቤት መቅረቡ ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ድል ነው በማለት በተለይ ከኢሳት ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ ይገልጻሉ።
እንደ ዲያቆን ተፈሪ ገለጻ ከሆነ ይህ የውሳኔ ሀሳብ ሲቀርብ በሰብአዊ መብት ጥሰት ከሚጠቀሱት ከነሰሜን ኮሪያ ጋር ኢትዮጵያን በመመደብ እንደሆነም አንስተዋል።
በዚህ ረቂቅ ላይ ከጸደቁት የህግ ሀሳቦች መካከል የሰርጊ ማግኔትስኪ አክት አንደኛው እንደሆነ የጠቀሱት ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ የሰርጊ ማግኔትስኪ አክት በሩሲያ ባለስልጣናት ላይ ተግባራዊ እንዲደረግ በአሜሪካ ምክር ቤት የጸደቀ ህግ እንደሆነም ተናግረዋል ።
በሌላ በኩል ይህ የህግ ሀሳብ በአሜሪካ ምክር ቤት እንዳይጸድቅ በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ በሚመራው መንግስት ከፍተኛ ዲፕሎማቶችና የማግባባት ስራ በሚሰሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ጭምር ከፍተኛ ስራ እየተሰራበት ሲሆን የውሳኔ ሀሳቡን ያቀረቡትን ኮንግረስ ማን ክሪስ ስሚዝን እስከ መደለል መድረሳቸውንም ለማወቅ ተችሏል።
ከኢሳት ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ዲያቆን ዮሴፍ ተፈራ ለኢትዮጵያውያን ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን የሀገሬ ጉዳይ ያገባኛል የገደኛል የሚል በተለይም የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው የአካባቢያቸውን ተወካይ በማነጋገር የውሳኔ ሀሳቡ በምክር ቤት እንዲጸድቅ ድጋፍ እንዲያደርጉ ማሳሰብ እንዳለባቸው ጠቅሰዋል።