ኤርትራ ጦሯን ከኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ማስወጣት ጀመረች
( ኢሳት ዜና ሃምሌ 11 ቀን 2010 ዓ/ም )ሬውተርስ እንደዘገበው ኤርትራ ጦሯን ከድንበር ማስወጣት የጀመረችው የቀረበውን የእርቅ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ያላትን ፍላጎት ለማሳየት ነው።
ምክትል ኢታማዦር ሹሙ ብርሃኑ ጁላ ኢትዮጵያም በተመሳሳይ መንገድ ጦሯን ከድንበር ለማስወጣት የጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድን ውሳኔ እየጠበቁ መሆናቸውን የኤርትራ ፕሬስ ዘግቧል። ኤርትራ ጦሯን ማስወጣቷ በአካባቢው ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ቁልፍ እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል።
በቅርቡ የሁለቱ አገራት መሪዎች አስመራንና አዲስ አበባን በጎበኙበት ወቅት በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ግጭት በይፋ መቆሙን ተናግረው ነበር።
ሀገራቱ የአየርና የትራንስፖርት አገልግሎቶችን ለመጀመር እንቅስቃሴዎችን እያደረጉ ሲሆን፣ የትራንስፖርት አገልግሎቱም በቅርቡ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።