ኤርትራ ህገመንግስት ይፋ ልታደርግ ነው
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 21 ቀን 2010 ዓ/ም ) የፕሬዚዳንቱ አማካሪ አቶ የማነ ገብረአብ እንደገለጹት ከኢትዮጵያ ጋር አዲስ መቀራረብ በመፈጠሩ ኤርትራ ህገ መንግስት በማርቀቅ ለህዝቡ አዳዲስ አማራጭ መንገዶችን ለማቅረብ ትሰራለች። ህዝቡ የፖለቲካ ተሳትፎ የሚያደርግበትን ሁኔታ ለመፍጠር እንሰራለን ያሉት አቶ የማነ፣ ህዝቡ በአገሩና በመንግስት አሰራር ዙሪያ የተሻለ ተሳትፎ ይኖረዋል ብለአል።
አገሪቱ በቅርቡ ህገመንግስት ማርቀቅ እንደምትጀመር የማስታወቂያ ሚኒስትሩ የማነ ገብረመስቀል አስታውቀዋል። ህገመንግስት የማርቀቁ ስራ በጦርነቱ ምክንያት ተቋረጦ እንደነበር የገለጹት አቶ የማነ፣ በአመቱ መጨረሻ ይፋ ይሆናል ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።