ኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አሜሪካ ገቡ።

ኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አሜሪካ ገቡ።
( ኢሳት ዜና ሃምሌ 19 ቀን 2010 ዓ/ም ) እንደ መንግስት መገናኛ ብዙሀን ዘገባ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋሽንግተን ዳላስ አየር ማረፊያ ሲደርሱ፣ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃንን ጨምሮ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሎስ አንጀለስ እና በዋሽንግተን ዲ ሲ በሚኖራቸው ቆይታ ከኢትዮጵያውያንና ትውልደኢትዮጵያውያን ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአሜሪካ ቆይታ የሚያደርጉት፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ፊታችን ሐምሌ 24 ቀን ድረስ ላሉት አምስት ቀናት ነው ።
ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዞ በአሜሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ተገናኝተውመወያየትን ዋና ዓላማው ያደረገ መሆኑን የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ዶክተር አቡይ ፦“ግንቡን እናፍርስ ድልድዩንም እንገንባ” በሚል መሪ ቃል የሚያደርጉት ጉዞ በአጠቃላይበአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፥ በሀገራቸው እየተካሄደ ላለው ሁለንተናዊለውጥ አካል ሆነው ለሀገሪቱ ልማትና እድገት አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ያለመ ነው ተብሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀምሌ 21 ቀን በዋሽንግተን ዲ ሲ እና ሀምሌ 22 ቀን በሎስ አንጀለስ ከተማዎች እንዲሁም ከዛ በኋላ በሚኒሶታ ሁሉም ወገኖች የሚሳተፉባቸው ጉባዔዎችን ያደርጋሉ።
ከተሞቹ በምስራቁና በምዕራቡ የአሜሪካ ግዛቶች የሚገኙእና ኢትዮጵያውያንን ወደ አቅራቢያ ማዕከልለማሰባሰብ አመች በመሆናቸው ለጉባኤው መመረጣቸው ተነግሯል።
በህዝባዊ ጉባዔው የፖለቲካ አመለካከት፣ ሀይማኖት፣ ብሄር፣ ወዘተ ሳይለያያቸው ሁሉም ኢትዮጵያውያን እናትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሳተፉም ጥሪ ቀርቧል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ከአቡነ መርቆርዮስ ጋር ተገናኝተው የሚወያዩ ሲሆን፥ ሁለቱ ሲኖዶሶችእያካሄዱ ባለው እርቀ ሰላም ላይ በቦታው በመገኘት ድጋፋቸውን እንደሚሰጡም ታውቋል።