ኢኮኖሚው ሰራዊቱን ሊሸከመው አልቻለም ተባለ

ግንቦት ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአገሪቱ ያለው የኢኮኖሚ ሁኔታ ሰራዊቱን ሊሸከመው አለመቻሉ የኢህአዴግ የ25 አመታት የመከላከያ አስተዳደር በሚገመገምበት ወቅት መነሳቱ ታውቛል። የአገሪቱ ኢኮኖሚ የሰራዊቱን ፍላጎት ማሙዋላት አለመቻሉ በሰራዊቱ ውስጥ እየተባባሰ ለመጣው ችግር ዋነኛ ምክንያት መሆኑ ተነግሯል።
የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት በስብስቡ እና አመራሩ በነባር ታጋዮች የተያዘ እና በጦር ካምፕ ብቻ ተነጥሎ የሚኖር ሰራዊት በመሆኑ ህዝባዊነት አልተላበሰም የሚል ትችት ቀርቦበታል። ሰራዊቱ ሙሉ በሙሉ ኢህአዴግዊ ባህርይ አለመላበሱም በውይይቱ ተገልጿል።