ታህሳስ 17 ቀን 2004 ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ሲኤን ኤን ሊጋተም ፕሮስፐርቲ ኢንዴክስን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ በአለም ላይ ደስታ የሚባል ነገር ከጠፋባቸው አገሮች መካከል ኢትዮጵያ ዝምባብዌና ማእከላዊ አፍሪካ የመጨረሻውን ደረጃ ይዘዋል።
ኖርዌይ፣ ዴንማርክና አውስትራሊያ ደግሞ በደስታ ብዛት ከአንድ እስከ ሶስት ያሉትን ደረጃዎች ይዘዋል።
ኢትዮጵያ የመጨረሻውን ደረጃ የያዘቸው በአገሪቱ ውስጥ በተንሰራፋው ስራ አጥነት፣ የመብት አፈናና የማህበራዊ አግልግሎት ችግር ነው።
ከህዝቡ ሲሶ የሚሆነው እንኳ በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት እንደማይደግፍ በሪፖርቱ ተጠቅሷል።
የመለስ መንግስት ላለፉት 7 አመታት የኢኮኖሚ እድገት እንዳስመዘገበ ሲገልጥ መቆየቱ ይታወቃል።