ኢትዮጵያ ለገለልተኛ የሰብአዊ መብት መርማሪዎች በሩዋን ክፍት እንድታደርግ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ

መስከረም (አሥራ ሦስ) ቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-በጄኔቫ ሲካሄድ በሰነበተው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ግምገማ ላይ አቋሙን ያስታወቀው አለማቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ኢትዮጵያ

የሰአብአዊ መብት ድንጋጌዎችን እንደምታከብር ቃል መግባት ብቻ ሳይሆን፣ በተጨባጭ ገለልተኛ ወገኖች እስር ቤቶችን እንዲገበኙ፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት የሚካሄዱባቸውን ቦታዎች እንዲጎበኙና በደል የደረሰባቸውን ወገኖች ለማነጋገር እንዲፈቀድላቸው ጠይቋል።

የሰብአዊ መብት ድርጅቱ ከዚህ ቀደም እንደታዩት ሁለት ምርጫዎች በዚህ አመት የሚካሄደውን ምርጫ ተከትተሎም ጋዜጠኞችን፣ ጸሃፊዎችንና ፖለቲከኞችን ማሰር መጀመሩን ገልጿል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ መንግስት ከቃል ባለፈ ተጨባጭ የሆነ የተግባር እርምጃ እንዲወስድ አለማቀፉ የሰብአዊ መብት ጉባኤግፊት ማድረግ እንደሚኖርበት መክሯል።

የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች የጸረ-ሽብር ህጉ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የሚመለከተው ህግ እንዲሰረዝ የሚያደርጉት ጫና ተቀባይነት እንደማይኖረው ገልጿል።