ታህሳስ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ብሉምበርግ እንደዘገበው ከአራቱም አገራት የተውጣጣ ኮሚቴ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከተቋቋመ በሁዋላ፣ በግድቡ ላይ ጥናት የሚካሂዱ ምሁራንንና ይመርጣል። ይህ ቡድን ጥናቱን ሲያጠቃልል ለሶስቱም መንግስታት የጥናት ውጤቱን ያቀርባል።
ከዚህ ቀደም የተቋቋመው አንድ አለማቀፍ ቡድን በግድቡ ፕሮጀክት ላይ ተጨማሪ ጥናት እንዲካሄድ ጠይቆ ነበር። ባለፈው ወር በሚቋቋመው ኮሚቴ ላይ አለማቀፍ ተወካዮች እንዲገኙ ግብጽ ያቀረበችውን ጥያቄ ኢትዮጵአ አልተቀበለችውም ነበር። አሁን ግብጽ አቋሟን መቀየሩዋንና ኮሚቴውን በሶስቱ አገሮች ወኪሎች ለማካሄድ መስማማቷን ዘገባው አመልክቷል። የሶስቱም አገራት ወኪሎች በጥር ወር መግቢያ ላይ እንደገና ሱዳን ላይ ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘዋል።