ጥር ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ተቀማጭነቱን እንግሊዝ ለንደን ያደረገው ሙቭኸብ የጥናትና ምርምር ተቋም በመላው ዓለም ባሉ አገራት በምግብ ወጪ ላይ ባደረገው ጥናት፣ ኢትዮጵያዊያን ኡጋንዳን በመከተል የሚያገኙት ወርሃዊ ደመወዝ አብዛኛውን ለምግብ ወጪ መሸፈኛ ያውሉታል።
ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ የያዙት የምስራቅ አፍሪካ አገራት ሲሆኑ፣ በጥናቱ መሰረት ኡጋንዳውያን 275.86 ከመቶ ገቢያቸውን ለምግብ በማውጣት ቀዳሚ ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያውያን 257.24 ከመቶ ወጪ በማውጣት 2ኛ ፣ ኬንያውያን ደግሞ 215.04 ከመቶ በማውጣት 3ኛ ሆነዋል።
የምግብ ፍጆታ ወጪያቸው አነስተኛ ከሆነባቸው አገራት ውስጥ ኳታር በቀዳሚነት ደረጃ ላይ ስትቀመጥ፣ ማካዎ 2ኛ ኩዌት 3ኛ ደረጃን ይዘዋል ።