ሐምሌ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአውስትራሊያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ኢትዮጵያዊው ወጣት ናስር ባሬ በሁለት የፖሊስ ባልደረቦች አካላዊ ጥቃትና የዘር መድሎ ተፈፅሞብኛል ብሎ ያቀረበው ክስ በወንጀል መርማሪዎች እንዲጣራ ትዕዛዝ አስተላልፏል
አቶ ናስር ”ሁለት ፖሊሶች ከፍሳሽ ትቦ ላይ አጋድመው ረገጡኝ ጥርሶቼ ተሰባብረዋል፣እጄን ጠምዝዘው ዐይኔ ላይ የሚያቃጥል ካፕሱም እስፕሬይ ረጩብኝ፣የጎን አጥንቶቼን ረገጠውኛል ይህ ሳያንሳቸው ፀያፍ የሆኑ የዘረኝነት ስድቦችን ይሰድቡኝም ነበር” በማለት ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።
የወጣቶች ጉዳይና የሰብዓዊ መብት ኃላፊ ቲፋኒ ኦቨርኦል ”በፖሊሶቹ ላይ የቀረበውን ክስ የሚያይ ገለልተኛ አጣሪ ቡድን ያስፈልጋል”ብለዋል።