ኢቦላ በኮንጎ በፍጥነት እየተስፋፋ መምጣቱ ተነገረ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 09 ቀን 2010 ዓ/ም) በዲሞክራቲክ ኮንጎ የታየው የኢቦላ ወረርሽኝ በፍጥነት እየተስፋፋ መምጣቱን የአገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ ኦሊይ ሊሉንጋ ካሌንጋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ በሽታው በገጠር ከታየ በሁዋላ፣ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ወደሚኖሩበት ምባንዳካ ከተማ ተዛምቷል።
በሽታው ወደ ዋና ከተማዋ ኪንሻ ይዛመታል የሚል ፍርሃት ማሳደሩም ተዘግቧል። እስካሁን ድረስ 42 ሰዎች መያዛቸው የተረጋጋጠ ሲሆን፣ ከተያዙት መካከል 23 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
ኢቦላ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ እጅገ አደገኛ በሽታ ነው። በፈረንጆች አቆጣጠር ከ2014-2016 በአፍሪካ በታየው ወረርሽን ከ11 ሺ በላይ ዜጎች ህይወታቸው አልፏል።