ኢሳት ወደ ኢትዮጵያ የሚያስተላልፈውን ስርጭት በተሻለ ሳተላይት ለማስተላለፍ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

ጥር 17 (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢሳት አስተዳደር እንደገለጸው የአሞስ የሳተላይት ስርጭት ለጊዜው በቴክንክ ችግር ምክንያት ቢቋረጥም፣  ቦርዱ ባወጣው ስታራቲጂካዊ እቅድ መስረት ኢሳት ስርጭቱን በአስተማማኝና በዘላቂ መንገድ ማስተላለፍ ይቻል ዘንድ ከልዩ ልዩ የሳተላይት ኩባንያዎች ጋር ተስማምቶ አገግሎቱን  ለኢትዮጵያ ህዝብ በስፋትና በጥራት  ለማድረስ እየሰራ ነው ብሎአል።

የኢሳት ሬዲዮናችን በአጭር ሞገድ በየቀኑ  በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ 3 ሰዓት በ 5 ፍሪክዌንሲ ገጠር ወረዳዎች ድረስ እየተሰማ መሆኑን፣ SES-5 የ24 ሠዓታት የቴሌቪዥን ፕሮግራም መቀጠሉንና በሌሎች ሁለት ሳተላይት ጣቢያዎች የ24 ሠዓታት የሬዲዮ ስርጭት በኢትዮጵያ እየተላለፈ እንደሚገኝ ገልጿል።

ቦርዱ የኢትዮጵያ ህዝብ በልዩ ልዩ ጊዜያት የኢሳትን የሳተላይት ስርጭት ለመከታተል ተጨማሪ ወጪ በማውጣት ጭምር የአገልግሎቶቹ ተጠቃሚ ለመሆን ላደርገውና ወደፊትም ለሚያደርገው ትብብር አድናቆቱን ገልጿል።