ኢሳት በሀረር የውሀ እጥረት መከሰቱን ከዘገባ በሁዋላ የክልሉ መስተዳደር በግምገማ እየታመሰ ነው

ጥቅምት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው ኢሳት በሀረር ስላለው የውሀ ችግር ዘገባ ማቅረቡን ተከትሎ የክልሉ መስተዳደር ግምገማ ተቀምጧል። ግምገማውን ተከትሎም የክልሉ የውሀ ልማት ሀላፊ ከስልጣን በመነሳት   እስር ቤት መግባታቸውን ለማወቅ ተችሎአል።

ግምገማው አሁንም ድረስ መቀጠሉን ለማወቅ ተችሎአል።

ኢሳት በሀረር ያለው የውሀ ችግር ማህበራዊ ተቃውሞ ሊያስነሳ እንደሚችል መዘገቡ ይታወሳል።