ጳጉሜን ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ አበባ ውስጥ በየ ቤቱ እየዞሩ ዲሽ የሚገጥሙ ወጣቶች ‹‹ኢሳትን እየቀጠላችሁ ነው›› በሚል ወከባ
እንደሚደርስባቸው መናገራቸውን ነገረ-ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡ጋዜጣው እንዳለው ወጣቶቹ ከኢሳት ውጭ ያሉ ጣቢያዎች የሚተላለፉበት ዲሽ ጭምር
በሚገጥሙበት ወቅትም ‹‹ኢሳትን እየቀጠላችሁ ነው፡፡ ህዝቡ ኢሳትን እንዲያይ ታደርጋላችሁ›› በሚል በደህንነቶች ወከባ እንደሚደርስባቸው ለጋዜጣው
ዝግጅት ክፍል ተናግረዋል፡፡ ከወራት በፊት መርካቶ አካባቢ ዲሽ የሚገጥሙ ወጣቶች ‹‹ኢሳትን ለህዝቡ እያሳያችሁ ነው›› ተብለው በፖሊስ ተይዘው እንደነበር
ጋዜጣው አስታውሷዋል፡፡ ያም ሆኖ በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ኢሳትን እንደሚገጥሙ የሚያሳዩ የዲሽ ማስታወቂያዎች በስፋት እንደሚታዩ ጋዜጣው
በምስል አስደግፎ ያቀረበው ዘገባ ያመለክታል።