ኢሳት (ጥቅምት 2 ፥ 2009)
ነዋሪነታቸው በዚህ በአሜሪካ ሚኒያፖሊስ ግዛት ሚኒሶታ ከተማ የሆነ ኢትዮጵያውያን ገቢው ኢሳትን ለመደገፍ የሚውል ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በቅርቡ አካሄዱ።
የኢሳትን ስድስተኛ አመት በማስመልከት በተካሄደው በዚህ ዝግጅት በርካታ ኢትዮጵያውያን በመታደም ኢሳት እያደረገ ያለውን መረጃ የማድረስ ጥረት በተለያዩ መንገዶች ለማገዝ ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየታቸውን የዝግጅቱ አስተባባሪ ለኢሳት አስታውቀዋል።
በዕለቱ የታደሙ ኢትዮጵያዊያን ከ62 ሺ ዶላር (ከአንድ ሚሊዮን ብር) በላይ በማሰባሰብ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን፣ የኢሳት የበላይ ስራ አስፈጻሚ ጋዜጠኛ አበበ ገላውና ፍቃዱ ሞረዳ በክብር እንግድነት በመገኘት የኢሳትን እንስቃሴ በተመለከተ ውይይት አካሄደዋል።
ተመሳሳይ የገቢ ማሰባሰቢያ በዚህ በአሜሪካ ሚዙሪ ካንሳስና ፕንስሌቨኒያ ግዛት በምገኘው የፊላዴልፊያ ከተማና ሌሎች ሃገራት እንደሚካሄድ የኢሳት አለም አቀፍ ገቢ ማሰባሰቢያ አስተባባሪ ኮሚቴ አስታውቋል።