(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 28/2010) የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ ኒዩክለር ማበልጸግ የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች እንዲጀምሩ ትዕዛዝ አስተላለፉ።
መንፈሳዊ መሪው አያቶላ ካሚኒ የሃገራቸው የኒዩክለር ማበልጸግ አቅምንም በሀገራቸው መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
የአሜሪካን ከኒዩክለር ስምምነቱ መውጣትን ተከትሎ ይህንን መልክዕት ያስተላለፉት መንፈሳዊ መሪው ሃገራቸው የኒኩለር መሳሪያ ካላቸው ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ ፍላጎታቸው መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ ሲ ኤን ኤን ዘገባ ከሆነ ኢራን ለመንግስታቱ ድርጅት የኒዩክለር ተቆጣጣሪ ተቋም በመጪው ማክሰኞ ታሳውቃለች።
የአውሮፓ ሃገራት በጉዳዩ ዙሪያ ፍራቻ እንዳላቸው የገለጸው ዘገባው ይህ ውሳኔዋ ኢራንን በነዳጅ ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚዋን ሊያሳጣት ይችላል ማለታቸው ተዘግቧል።