ኢህአዴግ በሆላንድ የጠራው ስብሰባ ከኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ገጠመው

የካቲት 19 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በአምስተርዳም ከተማ  የተጠራው የኢህአዴግ ስብሰባ ከቀኑ 7፡ሰ ዓት ተኩል ላይ እንደሚጀመር መረጃ የደረሳቸው ኢትዮጵያውያን፤ ልዩ ልዩ መፈክሮችንና  የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በመያዝ በስፍራው የተገኙት፤ ከስብሰባው መጀመር 30 ደቂቃ ቀድመው ነበር። 

“የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!ጋዜጠኞች ይፈቱ! የመሬት ንጥቂያ  በአስቸኳይ ይቁም! ሞት ለዜናዊ! መለስና ግብረ አበሮቹ ለፍርድ ይቅረቡ! እና ምዕራባውያን መለስን መደገፍ አቁሙ!”የሚሉት፤ ፤በሰልፈኞቹ ከተስተጋቡት መፈክሮች ጥቂቶቹ ናቸው። 

ጥቂት ቆይቶም የስብሰባው አስተባባሪዎች ወደ መሰብሰቢያ አዳራሹ ሲደርሱ በመታየታቸው፤ ኢትዮጵያውያኑ ሰልፈኞች ተቃውሟቸውን ማሰማት ጀመሩ። 

የሰልፈኞቹ ተቃውሞ እየጠነከረ በመምጣቱም በስብሰባው ለመካፈል ወደ ስፍራው ከደረሱት አንዳንድ የኢህአዴግ ደጋፊዎች መካከል ጥቂቶቹ ወደ አዳራሹ ሲገቡ፤አንዳንዶቹ ደግሞ ሳይገቡ ወደ መጡበት ተመልሰዋል። 

የስብሰባው መሪ የሆኑት በቤንሉክስ አገሮች ማለትም በቤልጅየም፣ በሆላንድና በሉክሰምበርግ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶክተር ካሱ ኢላላ ስብሰባው ይጀመራል ከተባለበት ሰዓት ለአንድ ሰዓት ያህል በመዘግየት ወደ ስፍራው ሲደርሱ፤በአዳራሹ ተገኝተው ሲጠባበቋቸው የነበሩት ታዳሚዎች ከ 15 አይበልጡም ነበር። 

ከዚህም በላይ፤ ቁጣ የተሞሉ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ እያሰሙ እንደሆነ መረጃው የተነገራቸው ዶክተር ካሱ፤ በሴኩሪቲዎች ታጅበውና በጓሮ በር በኩል አድርገው የሩጫ ያህል በመገስገስ ወደ አዳራሹ ሲገቡ ታይተዋል።

ዶክተር ካሱን በጓሮ በር ሲገቡ ያዩዋቸው ኢትዮጵያውያንም ከሁላ ከሁላ እየተከተሉ ፦”ካሱ ባንዳ!ካሱ ሆዳም!”ሲሏቸው ተደምጠዋል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide

 

ዶክተር ካሱ በስፍራው ተገኝተው ወደ አዳራሹ መዝለቃቸውን ተከትሎ ከውጪ  የኢትዮጵያውያኑ ተቃውሞ እያየለ በመምጣቱ፤ የተገኙት ጥቂት ሰዎችም ቢሆኑ መሰብሰብ ተስኗቸው ለረዥም ሰ ዓታት እየተፈራረቁ በመስኮት በማጮለቅ የተቃውሞ ሰልፈኞቹን ሲመለከቱ ተስተውለዋል።

 

በሁኔታው ከፍተኛ ብስጭት ያደረባቸው የስብሰባው አስተባባሪዎችም ወደ ሆላንድ ፖሊስ በመደወል ስብሰባቸው በጉልበተኞች እየተረበሸ እንደሆነና ሰልፈኞቹ ለስብሰባ የመጡ ሰዎችን እንዳይገቡ እየከለከሉ እንደሆነ በማመልከታቸው፤ በስፍራው የሆላንድ ፖሊስ ባልደረቦች ደረሱ።

 

ይሁንና ፖሊሶቹ  በስፍራው ደርሰው ሁኔታውን ከተከታተሉ በሁዋላ ፦”መስመራቸውን ጠብቀው መቃወም መብታቸው ነው”የሚል ምላሽ በመስጠታቸው፤ የስብሰባው አዘጋጆች ያቀረቡት ክስ ተቃባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።

 

በመሆኑም ኢትዮጵያውያኑ የተቃውሞ ድምፃቸውን አጠንክረው ማሰማታቸውን በመቀጠላቸው፤ኢህአዴግ በሆላንድ “ለዓባይ ግድብ “በሚል ሀሳብ ገንዘብ ለማሰባሰብ ሊያደርገው አቅዶት የነበረው ታላቅ ስብሰባ ከ 30 በማይበልጡ ካድሬዎች ሊካሄድ ግድ ሆኗል።