የካቲት ፫(ሦስት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-መጪውን ምርጫ ተከትሎ እያንዳንዱን መራጭ የሚቆጣጠርበትን ፎርም አዘጋጅቶ ለአባላቱ በድብቅ ያሰራጨው ኢህአዴግ፣ እያንዳንዱ አባል ከምርጫ ቦርድ የተመዝጋቢውን ስም ዝርዝር በመውሰድ ስለመራጩ ባህሪ፣ የፖለቲካ አቋምና ብሄር በዝርዝር ሞልቶ እንዲያስረክብ ያዛል።
የዚሁ ፎርም ቅጅ ኢሳት እጅ የገባ ሲሆን፣ ፎርሙ መራጮች ወደ ምርጫ ጣቢያ ከመሄዳቸው በፊት ኢህአዴግ አስቀድሞ የሚቆጣጠርበትን መንገድ ያመቻችለታል፡፡ የኢህአዴግ ካድሬዎች የመራጩን ማንነት ካወቁ በሁዋላ የአካባቢ ሹሞች ወደ መራጩ ቤት በመሄድ በማስፈራራት ኢህአዴግን እንዲመርጥ እንደሚያደርጉት የኢህአዴግ ካድሬዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የሚደረገውን ምርጫ በመታዘብ ገንዘብና ጊዜ እንደማያጠፋ ማስታወቁ ይታወሳል።