መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በኢሲኤ የስብሰባ አዳራሽ የቀረበው የተመድ ሪፖርት እንደሚያሳዬው በተያዘው አመት መጨረሻ በአፍሪካ 4 ነጥብ 5 በመቶ እድገት ሊገኝ ይችላል። ከሁለት አመት በፊት በአህጉሪቱ የታየው የ5 በመቶ እድገት አምና በአለም ላይ ከተፈጠረው የኢኮኖሚ ቀውስንና ከአረቡ አብዮት ጋር ተያይዞ በዚህ አመት ሊደገም አለመቻሉ በሪፖርቱ ተመልክቷል።
በአህጉሪቱ እየጨመረ የመጣው ስራ አጥነት የአገራትን ሰላምና ደህንነት አደጋ ውስጥ እንደጣለው በሪፖርቱ ተመልከቷል።
የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት በከፍተኛ ደረጃ ሊቀንስ እንደሚችል ተመልክቷል። በአገሪቱ ውስጥ የሚታየው የዋጋ ንረት አሳሳቢ መሆኑም ተጠቅሷል ።
አይኤም ኤፍ ኢትዮጵያ በያዝነው አመት 5 በመቶ የሚሆን እድገት ልታስመዘገብ እንደምትችል መተንበዩ ይታወቃል። የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ እድገቱ 11 በመቶ ይሆናል በማለት የአይኤም ኤፍን ትንበያ ያጣጥላል።
የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ የታየው የሁለት ወራት የተዳከመ የስራ እንቅስቃሴ፣ እንዲሁም አለመረጋጋት ይፈጠራል በሚል ስጋት ባለሀብቶች ሀብታቸውን ማሸሽ መጀመራቸው የዘንድሮውን እድገት ከ5 በመቶ በታች ሊያወርደው እንደሚችል ይገመታል።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide