አፍሪካ ቫኬሽን የመዝናና ሆቴል ከባድ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ደረሰበት

ኢሳት (የካቲት 22 ፥ 2008)

በደቡብ ክልል ሃዋሳ ከተማ ላንጋኖ ሃይቅ ዳርቻ የተገነባውና የባለ አምስት ኮከብ ደረጃ ያለው አፍሪካ ቫኬሽን የመዝናኛ ሆቴል ሰኞ ምሽት ከባድ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ደረሰበት።

ምክንያቱ ባልታወቀው በዚሁ የእሳት ቃጠሉ የሆቴሉ የማረፊያና ሌሎች ክፍሎች ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው እማኞች ዋቢ በማድረግ በሃገር ውስጥ ያሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በዚሁ የመዝናኛ ሆቴል ላይ በአጠቃላይ የደረሰው ጉዳት ለማወቅ የተደረገ ጥረት ያልተሳካ ሲሆን፣ የእሳት ቃጠሎን ተከትሎም ሆቴሉ ስራውን እንዳቋረጠ ተገልጿል።

ከአስር አመት በፊት በሃገር ውስጥና በውጭ ባለሃብቶች በሽርክና የተቁቋመው አፍሪካ ቫኬሽን ከኦሮሚያ ክልል መንግስት በተረከበውን 45ሺ ስኩዌር ሜትር ላይ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመያዝ ስራውን እንደጀመረም ለመረዳት ተችሏል።