ጥቅምት ፲፰ (አሥራ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መነሻቸውን የሊቢያዋ ታጁራ የባህር ዳርቻዎች አድርገው ወደ አውሮፓ ሲጓዙ ከነበሩ አፍሪካዊያን ስደተኞች መካከል ቁጥራቸው ከ90 በላይ የሚሆኑት ሕይወታቸውን ማጣታቸውን የሊቢያ ባሃር ሃይልን ጠቅሶ አልጀዚራ ዘግቧል።
የሊቢያ የባሕር ሃይል ቃል አቀባይ የሆኑት አዩብ ቃሲም ፣ ስደተኞቹ እርዳታ እንዲደረግላቸው በጠየቁት መሰረት ቁጥራቸው 126 ከሚገመቱት ተጓዦች መካከል የተወሰኑትን ታድገናል ብለዋል። በያዝነው ዓመት ብቻ ቁጥራቸው ከ3 ሺ 800 በላይ የሚሆኑ ስደተኞች በሜዲትራኒያን ባህር ውስጥ መሞታቸውን እና ባለፈው ዓመትም በተመሳሳይ ከ3 ሺ 771 በላይ ስደተኞች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን አልጀዚራ አክሎ ዘግቧል።