አፍሪካዊያን ስደተኞች በየመን ባለስልጣናት ግድያ፣ ሰቆቃና መደፈር ይፈጸምባቸዋል ሲል ሂውማን ራይትስ ወች አስታወቀ

አፍሪካዊያን ስደተኞች በየመን ባለስልጣናት ግድያ፣ ሰቆቃና መደፈር ይፈጸምባቸዋል ሲል ሂውማን ራይትስ ወች አስታወቀ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 10 ቀን 2010 ዓ/ም) አፍሪካዊያን ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞች ላይ ኢሰብ ዓዊ በሆነ ሁኔታ መብቶቻቸውን በመጣስ ግድያ፣ ሰቆቃና መደፈር ይፈጸምባቸዋል ሲል ሂውማን ራይትስ ወች መግለጫ አወጣ። በሰሜናዊ የመን በምትገኘው የባህር ወደብ ከተማ በሆነችው አደን ለምስራቅ አፍሪካዊያን ስደተኞች በተናጠል በእስር ቤት ውስጥ እንዲታሰሩ ተደርገዋል።
በእስር ቤቱ ያሉት ጥገኝነት ጠያቂዎችና ወደ አገራቸው ተመላሽ ስደተኞች ያሉበት የባሕር ዳርቻ እጅግ አሳሳቢ ከመሆኑ በተጫማሪ በባለስልጣናቱ ሰብዓዊ መብታቸውን ተገፈዋል። በስደተኞቹ ላይ ድብደባ፣ አስገድዶ መድፈር፣ በአስገዳጅ ሁኔታ በጅምላ ወደ አገራቸው መመለስና በተደረሰባቸው ድብደባና እንግልት ሕይወታቸውን ያጡ እንደሚገኙበት ገዳተኞቹን በማነጋገር ማረጋገጡንና አሁንም ያሉበት ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል ሲል ሂውማን ራይትስ ወች አስታውቋል። ይህንን የስደተኞች የመብት ጥሰቶች አስመልክቶ ባለስልጣናቱ ማስተባበያ ሰጠዋል።
በየመን ባለስልጣናት ወደ አገራቸው የሚመለሱ ስደተኞች ተገለዋል፣ የእስር ቤቱ ጠባቂዎች ሴት ስደተኞችን ላይ የግዳጅ ወሲብ ፈጽመዋል፣ በገመድ በማሰር አሰቃይተዋል፣ ገንዘባቸውንና ንብረታቸውን ይዘረፋሉ፣ የተመድ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዶክመንቶታቸውንም ይነጠቃሉ።
”አደን የሚገኘው እስር ቤት ጠባቂዎች ወንድ እስረኞችን በጭካኔ ይደበድባሉ። ሴቶችን ሕጻናትን ይደፍራሉ፣ በተጨናነቀ ጀልባዎች በግዳጅ በባህር ታጭቀው ወደ አገራቸው ይመለሳሉ። የመን ያለው የአገሪቱ ውድቀት ይህን አስቀያሚ የመብት ጥሰቶች ለማስቆም እንዳይቻል አድርጎታል። የየመን መንግስት ለዚህ ሁሉ የመብት ጥሰቶች ተጠያቂዎች ናቸው።” ሲሉ የሂውማን ራይትስ ወች ዳሬክተር የሆኑት ቢል ፍርሊክ ተናግረዋል። አብዛሃኞቹ ስደተኞች ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ታውቋል።